ትሬቤታ
Appearance
ትሬቤታ በጌስታ ትሬቬሮሩም ዘንድ የትሪር ከተማ (በአሁኑ ጀርመን) አፈታሪዊ መስራች ነበር። የአሦር ንጉሥ ኒኑስ ልጅ እንደ ነበር ኒኑስ ንግሥቱን ሴሚራሚስን ሳያግባ በሆነችው ሚሥት እንደ ተወለደ ተጻፈ። የአባቱ ንግሥት ሴሚራሚስ ጠላችውና በኋላ መንግሥቱን በያዘች ጊዜ ትሬቤታ ከአሦር ወጥቶ ወደ አውሮጳ ሔደ። ከጊዜ በኋላ ከሠፈረኞች ጋር በትሪር ተቀመጠ።
ዮሐንስ አቬንቲኑስ እንደ ጻፈው ግን ትሬቤታ (ትራይበር ወይም ትሬቬር) የኒኑስ ልጅ ሳይሆን በእውነት የጀርመን 2ኛው ንጉሥ የማኑስ ልጅ ነበረ። አቬንቲኑስ እንዳለው ይህ ትሬቤታ ደግሞ ከተሞች በመትዝና ስትራዝቡርግ (አሁን በፈረንሳይ)፣ ማይንጽ፣ ስፓየርና ቩርምዝ (በጀርመን) እና ባዝል (በስዊስ) መሠረተ። ይህ ምናልባት 2213 ዓክልበ. ግድም ይሆን ነበር።